አስቸኳይ ማስታወቂያ ለስራ ፈላጊዎች
በፀጋህ የህክምና አገልግሎት ኃ/የተ/የግ ማህበር BETSEGAH MEDICAL SERVICE P.L.C
በፀጋህ የእናቶችና የህፃናት ሆስፒታል ሀገር ወዳድ በሆኑ ኢትዮጵያዊያን የተቋቋመ መንግስታዊ ያልሆነ ሆስፒታል ነው፡፡ ሆስፒታሉ የኢትዮጵያን እናቶችና ህፃናት ማህበራዊና የጤና ሁኔታ ለማሻሻል በሚደረገው ሀገራዊ ተሳትፎ የበኩሉን አስተዋፅኦ ለማድረግ የተመሠረተ ሲሆን፤ ከዚህ በታች ባሉት ክፍት ቦታዎች ብቁ የሆኑ አመልካቾችን አወዳድሮ ለመቅጠር ይፈልጋል፤
1ኛ – የስራ መደቡ መጠሪያ፡- ክሊኒካል ነርስ (Clinical Nurse)
ተፈላጊ የትምህርት ደረጃ፡- በክሊኒካል ነርስ ዲፕሎም
የሥራ ልምድ፡- 2 ዓመት የስራ ልምድና ከዚያም በላይ
ደመወዝ ፡- በሆስፒታሉ ስኬል መሠረት
2ኛ – የስራ መደቡ መጠሪያ፡– ሂሳብ ሠራተኛ (Accountant)
ተፈላጊ የትምህርት ደረጃ፡- በሂሳብና መዝገብ አያዝ (Accounting)
የሥራ ልምድ፡- ለዲፕሎም 3 ዓመትና ከዚያ በላይ
3ኛ – የስራ መደቡ መጠሪያ፡- የእንግዳ ተቀባይ ክፍል ፋላፊ
ተፈላጊ የትምህርት ደረጃ፡- በእንግዳ አቀባበል፣ በሴክሬተሪ እና በአይቲ ዲፕሎም/ዲግሪ በኃላፊነት የሠራ
የሥራ ልምድ፡- ለዲግሪ 3 ዓመት ለዲፕሎም 5 ዓመትና ከዚያ በላይ ሆኖ 2ቱን ዓመት በኃላፊነት የሠራ፣ የማስተባበርና የመምራት ልምድና ችሎታ ያለው፡፡
4ኛ – የስራ መደቡ መጠሪያ፡- እንግዳ ተቀባይ
ተፈላጊ የትምህርት ደረጃ፡- በእንግዳ አቀባበል፣ በሴክሬተሪ እና በአይቲ ዲፕሎም / ዲግሪ
የሥራ ልምድ፡- ዲፕሎም 3 ዓመት / ዲግሪ 2 ዓመትና ከዚያ በላይ
ደመወዝ፡- ለሁሉም የሥራ መደቦች በሆስፒታሉ ስኬል መሠረት ይሆናል፡፡
የሥራ ቦታ፡- ቦሌ ክ/ከተማ፣ ወረዳ 4፣ ቅዱስ ዑራኤል ቤተክርስቲያን ወደ ፒኮክ የሚያስገባው መንገድ ላይ አትላስ ሆቴል ሳይደርሱና ድልድዩን ሳይሻገሩ ነው፡፡